ክላውዲዮ ራኔሪ የሮማ አሠልጣኝ ኾኑ።

0
161

ባሕር ዳር: ኀዳር 05/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ጣሊያናዊ አሠልጣኝ ራኔሪ አዲሱ የሮማ አሠልጣኝ በመኾን ተሹመዋል።

ሮማ በውጤት ማጣት አሠልጣኙ ኢቫን ዩሪችን አሰናብቷል። ይህን ተከትሎ ክለቡ አዲስ አሠልጣኝ ሲፈልግ ቆይቷል። አሁን አንጋፋው ክላውዲዮ ራኔሪን አሠልጣኝ ማድረጉን ቢቢሲ በስፖርት ገጹ ጽፏል።

ራኔሪ በተለያዩ ክለቦች ለረዥም ዓመታት በአሠልጣኝነት ሥራ አሳልፈዋል። በተለይ ሌስተር ሲቲን እየመሩ የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ዋንጫን ባነሱበት ታሪካቸው በእግር ኳሱ ዓለም ይታወሳሉ።

ከአሠልጣኝነት መገለላቸውን ይፋ ካደረጉ ከስድስት ወራት በኋላ ነው ክላውዲዮ ራኔሪ እንደገና ወደ አሠልጣኝነት የተመለሱት።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here