ባሕር ዳር: ጥቅምት 28/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የዩሮፓ ሊግ ጨዋታዎች ዛሬ ምሽት በተለያዩ የአውሮፓ ሀገራት ይካሄዳሉ። ከሚከናወኑ ጨዋታዎች መካከል ማንቸስተር ዩናይትድ ከግሪኩ ፖኦክ ጋር የሚያደርገው ጨዋታ ይጠበቃል።
ማንቸስተር ዩናይትድ በጊዚያዊ አሠልጣኙ ሩድ ቫርኔስትሮይ እየተመራ በሁለት ጨዋታዎች ጥሩ የሚባል ጉዞ ላይ ነው። በዩሮፓ ሊጉ በሦስት ጨዋታ ሦስት ነጥብ ብቻ የያዘው ዩናይትድ በዛሬው ጨዋታ ማሸነፍ ግድ ይለዋል።
አዲሱ ፈራማ ሊኒ ዩሮ ለጨዋታው ብቁ መኾኑ ሲረጋገጥ ኤሪክሰን፣ ማውንት እና አንቶኒ ጉዳት ላይ መኾናቸውን የቢቢሲ መረጃ እማኝ ነው።
ላዚዮ ከፖርቶ፣ ጋላታሳራይ ከቶትንሃም እና ኤዜድ አልካማር ከፌነርባቼ የሚያደርጓቸው ጨዋታ ከበርካታ መርሐ ግብሮች ተጠባቂዎቹ ናቸው።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!