የካፍ ቀጣናዊ የእግር ኳስ ማኅበራት ስብስባ ተጀመረ።

0
197
ባሕር ዳር: ጥቅምት 10/2017 ዓ.ም (አሚኮ)የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን ቀጣናዊ የእግር ኳስ ማኅበራት ስብስባ ዛሬ በአዲስ አበባ ተጀምሯል።
ስብስባው ለሁለት ቀናት ሲቆይ 46ኛው የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) ጠቅላላ ጉባዔ ጥቅምት 12/2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ ተገልጿል፡፡
ከጉባዔው ጎን ከጎን የተለያዩ ሁነቶች በመካሄድ ላይ እንደሚገኙም ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ከመርሐ ግብሮቹ አንዱ የካፍ ቀጣናዊ የእግር ኳስ ማኅበራት የሚያካሂዷቸው ስብስባዎች ናቸው።
የደቡብ አፍሪካ እግር ኳስ ማኅበራት ምክር ቤት፣ የምዕራብ አፍሪካ እግር ኳስ ማኅበር “ኤ” ዞን፣ የምዕራብ አፍሪካ እግር ኳስ ማኅበር “ቢ” ዞን፣ የምስራቅ እና መካከለኛው አፍሪካ እግር ኳስ ማኅበራት ምክር ቤት እና የማዕከላዊ አፍሪካ እግር ኳስ ፌዴሬሽኖች ማኅበር ዛሬ ስብስባቸውን ያደርጋሉ።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here