ባሕር ዳር: ጥቅምት 06/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ጀርመናዊ አሠልጣኝ የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድንን ለመረከብ ከስምምነት ደረሰዋል። ከቀጣዩ ጥር ወር የሚጀምር እና እንደ አውሮፓዉያን አቆጣጠር ሀምሌ 2026 በሚጠናቀቅ ውል ነው ብሔራዊ ቡድኑን ለመረከብ የተስማሙት።
በቢቢሲ መረጃ መሰረት አሠልጣኙ እና የእንግሊዝ እግር ኳስ ማኅበር በሁሉም ነገር ተስማምተዋል። የሚቀረው መፈራረም እና ጉዳዩን ይፋ ማድረግ ብቻ ነው። በዚህም ቱሸል የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድንን በማሠልጠን የመጀመሪያው ጀርመናዊ ለመኾን ተቃርበዋል።
ከሴቨን ጎራን ኤሪከሰን እና ፋብዮ ካፔሎ በመቀጠልም ሦስተኛው እንግሊዛዊ ያልኾኑ የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድንን የመሩ ይኾናሉ።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!