ባሕር ዳር: ጥቅምት 06/2017 ዓ.ም (አሚኮ)
አርጀንቲናዊ ኮከብ ሊዮኔል መሲ ከብሔራዊ ቡድን ጨዋታዎች በጉዳት ርቆ ነበር። ነገር ግን በዓለም ዋንጫ ማጣሪያ አርጀንቲና ከቦሊቪያ በነበረው ጨዋታ መሰለፍ ችሏል።
ሌሊት ከቦሊቪያ ጋር የነበረባትን ጨዋታ አርጀንቲና 6 ለ 0 አሸንፋለች። መሲ ሀትሪክ የሠራ ሲኾን ሁለት ግብ የኾኑ ኳሶችን ደግሞ አቀብሏል።
በተጨማሪም የጨዋታው ኮከብ ተብሎ የተመረጠው መሲ በህይወት ዘመኑ ያስቆጠራቸውን ግቦች ብዛትም 846 ደርሰዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!



