ባሕር ዳር: ጥቅምት 05/2017 ዓ.ም (አሚኮ)የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የምድብ አራተኛ ጨዋታውን ከጊኒ ጋር ያደረገው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን 3 ለ 0 ተሸንፏል።
ሴሪሁ ጉራሲ (2 ግብ) እና አብዱላሂ ቱሬ የጊኒን ሦስት የማሸነፊያ ግቦች ማስቆጠር ችለዋል።
ውጤቱን ተከትሎ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በ1 ነጥብ 4ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። የጊኒ ብሔራዊ ቡድን ደግሞ በ6 ነጥብ 2ኛ ደረጃን ይዟል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!