ቶማስ ቱሸል ቀጣዩ የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን አሠልጣኝ ለመኾን ቀዳሚ ተመራጭ ኾነዋል።

0
257

ባሕር ዳር: ጥቅምት 05/2017 ዓ.ም (አሚኮ)

ጀርመናዊ አሠልጣኝ ቶማስ ቱሸል የእንግሊዝ ብሔራዊ ብድን አሠልጣኝ የመኾን ሰፊ እድል እንዳላቸው ስካይ የመረጃ ምንጭ ጽፏል። አሠልጣኙ በእንግሊዝ ቼልሲን፣ በፈረንሳይ ፒኤስጅን እና በጀርመን ቦሩሲያ ዶርትሙንድን የመሳሰሉ ታላላቅ ክለቦችን አሠልጥነዋል።

የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ከአሠልጣኝ ጋሬት ሳውዝጌት ጋር ከተለያየ በኋላ በጊዚያዊ አሠልጣኝ እየተመራ ይገኛል። ዋና አሠልጣኝ ለመቅጥር አማራጮችን እያየ የሚገኘው የሀገሪቱ የእግር ኳስ ፌዴሬሽን በዋናነት ፔፕ ጋሪዲዮላን ለመቅጥር ጽኑ ፍላጎት ነበረው።

ነገር ግን ስፔናዊ አሠልጣኝ ሲቲን በአጭር ጊዜ ይለቃል ተብሎ ስለማይጠበቅ ቱሸል ከሌሎች አማራጮች ቅድሚያ ተመራጭ መኾናቸውን ዘገባው አትቷል።

ቶማስ ቱሸል በማንቸስተር ዩናይትድ ቤት ቴንሀግን ለመተካት ተቃርበዋል የሚል ወሬዎች ሲናፈሱ እንደነበር ይታወሳል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here