ባሕር ዳር: ነሐሴ 07/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የስፔኑ አትሌቲኮ ማድሪድ ጁሊያን አልቫሬዝን ከማንቸስተር ሲቲ ላይ በ81 ነጥብ 5 ሚሊዮን ፓውንድ አስፈርሟል፡፡ ማንቸስተር ሲቲ የ24 ዓመቱን አርጀንቲናዊ አጥቂ ለአትሌቲኮ ማድሪድ የሸጠበት ገንዘብ የሳምንቱ ውድ ዋጋ መኾኑን ዴይሊ ሜይል ስፖርት ዘግቧል፡፡
አልቫሬዝ እንደ አውሮፓ አቆጣጠር ከ2018 እስከ 2024 በአርጀንቲናው ሪቨር ፕሌት እና በእንግሊዙ ማንቸስተር ሲቲ ቡድኖች ቆይታው በ141 ጨዋታዎች ተሰልፎ 54 ግቦችን ማስቆጠር ችሏል፡፡ ለሀገሩ አርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን ደግሞ በተለያዩ የዕድሜ ደረጃዎች በ62 ጨዋታዎች ተሰልፎ 12 ግቦችን አስቆጥሯል፡፡
ተጫዋቹ በማንቸስተር ሲቲ ያደረገው ቆይታ ጥሩ እንደነበር ገልጾ “በቡድኑ በነበርኩበት ጊዜያቶች ያገኘሁት ትምህርት የቀጣይ ሕይዎቴን መንገድ አመቻችቶልኛልና አመሠግናለሁ” ማለቱን የዘገበው ዩሮ ስፖርት ነው፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!