ባሕር ዳር: ነሐሴ 6/2016 ዓ.ም (አሚኮ)በፓሪስ 2024 ኦሎምፒክ ለተሳተፉ እና ውጤት ላስመዘገበው የልዑካን ቡድን ነሐሴ 7/2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 12፡00 ሰዓት ላይ በቦሌ ዓለም አቀፍ አየር መንገድ አቀባበል እንደሚደረግ የባሕል እና ስፖርት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
በዕለቱ ከሰዓት በኋላ በብሔራዊ ቤተ መንግሥት ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በተገኙበት የክብር ሽልማት፣ የማበረታቻ እና የእራት ግብዣ መርሐ ግብር እንደሚካሄድ ሚኒስቴሩ ገልጿል፡፡
እንደ ኢቢሲ ዘገባ ኢትዮጵያ በ33ኛው የፓሪስ ኦሎምፒክ አንድ የወርቅ እና ሦስት የብር በአጠቃላይ አራት ሜዳሊያዎችን በመሠብሠብ ከዓለም 47ኛ ከአፍሪካ ደግሞ አራተኛ ደረጃን ይዛ ማጠናቀቋ ይታወቃል፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!