አጫጭር የስፖርት ዜናዎች

0
307

ባሕር ዳር: ነሐሴ 06/2016 ዓ.ም (አሚኮ)-አሠልጣኝ ጆዜ ሞሪንሆ በቱርክ ሊግ የመጀመሪያ ጨዋታ ካርድ ተመልክተዋል። ፖርቱጋላዊ አሠልጣኝ ክለባቸው ፌነርባቼ በቱርክ ሊግ የመጀመሪያ ጨዋታን 1 ለ 0 ባሸነፈበት ጨዋታ ከአራተኛ ዳኛ ጋር እሰጣ ገባ ውስጥ ገብተው ገና በ20 ኛው ደቂቃ የማስጠንቀቂያ ካርድ መመልከታቸውን ሚረር አስነብቧል።

-አሮን ዋን ቢሳካ ዌስትሃምን ለመቀላቀል ጫፍ ደርሷል። ስምምነቶቹ ተደርሰው የተጫዋቹ የህክምና ምርመራ ብቻ ቀርቷል። በስካይ ስፖርት መረጃ መሰረት ዌስተሃም ለተጫዋቹ ዝውውር 15 ሚ ፓውንድ ለዩናይትድ ይከፍላል።

-ማንቸስተር ዩናይትድ ከባየርሙኒክ ማቲያስ ዲሊት እና ኑሲር ማዝራውይን በአጭር ጊዜ ውስጥ የግሉ እንደሚያደረግ ቢቢሲ አስነብቧል። ተጫዋቾቹ ከዩናይትድ ጋር ስማቸው ከተያያዘ ወራት ተቆጥረዋል።

-ቼልሲ ፔድሮ ኔቶን ማስፈረሙን አረጋግጧል። ለተጫዋቹ ዝውውር 54 ሚ ፓውንድ ለወልብስ መክፈሉም ተረጋግጧል።

-አርሰናል ኪንግስሊ ኮማንን ለማስፈረም እንቅስቃሴ ጀምሯል። ኮማን በሙኒክ ቤት ተመራጭ ባለመኾኑ ከክለቡ እንዲ ወጣ ይፈለጋል። አርሰናል ኮማንን በውሰት ማስፈረም እንደሚፈልግ ነው ፉትቦል ኢንሳይድር ያስነበበው።

-አሌክስ ሳንቸዝ የቀድሞ ክለቡን ተቀላቅሏል። ሳንቸዝ ለባርሴሎና፣ አርሰናል፣ ማንቸስተር ዩናይትድ እና ኢንተር ሚላንን ለመሳሰሉ ክለቦች ተጫውቷል። በአውሮፓ የመጀመሪያ ክለቡ ግን የጣሊያኑ ዩዲንዜ ነው። ችሊያዊ አጥቂ ከዓመታት በኅላ አሁን ዩዲንዜን ተቀላቅሏል።

-ባርሴሎና ሰርጅዮ ሮቤርቶ ከክለቡ መሰናበቱን አስታውቋል። የላማሲያ ውጤት የኾነው ሮቤርቶ በባርሴሎና ቤት 25 የሚደርሱ ዋንጫዎችን አሳክቷል።

-የሻምፒዮን ሽፑን ፕላይ ማውዝ የሚያሠለጥነው ዋይኒ ሮኒ በመጀመሪያ የነጥብ ጨዋታው ሽንፈት ገጥሞታል። በሩኒ የሚመራው ፕላይዝ ማውዝ በሸፊልድ ወይንስ ዳይ 4 ለ 0 መሸነፉን የቢቢሲ መረጃ ያሳያል። ሩኒ ስኬታማ የተጫዋችነት ጊዜን ቢያሳልፍም በአሠልጣኝነት ግን በተለያዩ ክለቦች ጥሩ ስም የለውም።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here