ዴቪድ ደሃያ ለፊሪዮንቲና ለመጫዎት ስምምነት ላይ ደርሷል።

0
197

ባሕር ዳር: ነሐሴ 03/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የቀድሞው የማንቸስተር ዩናይትድ ግብ ጠባቂ ዴቪድ ደሃያ ከአንድ ዓመት በላይ ያለ ክለብ ቆይቷል። ተጫዋቹ ከዩናይትድ ቤት ከወጣ በኅላ አዲስ ክለብ ሲፈልግ ቆይቷል። ነገር ግን በጎል መረጃ መሰረት ስፔናዊ ተጫዋች አሁን ላይ የጣሊያኑን ፊሪዮንቲና ለመቀላቀል ጫፍ ደርሷል።

የጣሊያኑ ክለብ ለቀድሞው የዩናይትድ ኮከብ የአንድ ዓመት ውል ሰጥቶታል። ተጫዋቹ ፊርማውን ለማኖር ወደ ጣሊያን ማምራቱንም ጎል ዘግቧል።

ደሃያ በማንቸስተር ዩናይትድ ቤት ወርቃማ ጊዜውን አሳልፏል። ፕሪምየር ሊግን ጨምሮ በርከት ያሉ ዋንጫዎችንም አንስቷል። ነገር ግን ብዙ ከተከበረበት ኦልድትራፎርድ በቴንሃግ ተገፍቶ መውጣቱን ሲገልጽ ተሰምቷል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here