ባሕር ዳር: ነሐሴ 03/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በፓሪስ 33ኛው የኦሎምፒክ ጨዋታዎች ዛሬ ማምሻውን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች የሚጠበቁበት የ10 ሺህ ሜትር ሴቶች የፍጻሜ ውድድር ይካሄዳል። ጉዳፍ ፀጋየ፣ አትሌት ፅጌ ገብረሰላማ እና አትሌት ፎትዬን ተስፋይ ወክለው ይሳተፋሉ።
ኢትዮጵያ እስካሁን የወርቅ ሜዳልያ ማስመዝገብ አልቻለችም። 2 ብር እስካሁን የተገኙ ሜዳሊያዎች ናቸው። ኢትዮጵያ ሜዳልያ ከምትጠብቃቸው ርቀቶች መካከልም የዛሬው 10 ሺህ ሜትር ተጠቃሽ ነው።
ውድድሩ ምሽት 3:57 የካሄዳል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!