አሜሪካ የኦሎምፒክ የሜዳሊያ ሰንጠረዡን እየመራች ነው።

0
274

ባሕር ዳር: ነሐሴ 02/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የፓሪሱ ኦሎምፒክ በብዙ ክስተቶች ታጅቦ ቀጥሏል። ያልተጠበቁ አሸናፊዎች እና የክብረወሰኖች መመዝገብ በስፋት እየታዩ ነው። ወዲህ ግን ወርቅ የለመደው የሀገሬ ሰው የፓሪስ ዝግጅት እስካሁን አልቀናውም። ውጤት ማጣቱን ተከትሎም በየቦታው ጉርምርምታዎች እየተሰሙ ነው።

ከዚህ በፊት ኢትዮጵያውያን በእርግጠኝነት ውጤት የሚያመጡባቸው ርቀቶች ዘንድሮ የሌሎች ሲሳይ እየኸኑ ነው። እስካሁን የተመዘገበው ሜዳልያ ብዛት ሁለት ብር ብቻ ነው። እንዲህ የቀጠለው የፓሪሱ ኦሎምፒክ በእስካሁን ጉዞው አሜሪካን በሜዳልያ ብዛት ቀዳሚ አድርጓል። ይህ ዜና እስከ ተሠራበት ጊዜ ድረስ አሜሪካ 27 ወርቅ፣ 35 ብር እና 33 ነሀስ በድምሩ 95 ሜዳልያ ሠብሥባለች። ቻይና 25 ወርቅ፣ 24 ብር እና 17 ነሀስ በድምሩ በ66 ሜዳልያ አሜሪካን እየተከተለች ነው።

ሦስተኛ ደረጃን አውስትራሊያ ይዛለች። 18 ወርቅ፣ 13 ብር እና 11 ነሀስ ደግሞ እስካሁን ያገኘችው የሜዳልያ ብዛት ነው። በቢቢሲ መረጃ መሰረት አራተኛ ደረጃ ላይ አዘጋጇ ፈረንሳይ፣ አምስተኛ ላይ ደግሞ ታላቋ ብሪታንያ ተቀምጠዋል። ወርቅ የጠማት ኢትዮጵያ ደግሞ በሁለት የብር ሜዳልያ 59ኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች። ኬንያ 1 ወርቅ፣ 1 ብር እና 3 ነሀስ ከአፍሪካ ሀገራት የተሻለችው ሀገር ናት።

በፓሪሱ ኦሎምፒክ እስካሁን 74 ሀገራት ሜዳልያ ማስመዝገብ ችለዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here