ባሕር ዳር: ነሐሴ 2/2016 ዓ.ም (አሚኮ)በ33ኛው የፓሪስ የኦሎምፒክ ኢትዮጵያውያን የሚሳተፉበት የ1 ሺህ 500 ሜትር የሴቶች ግማሽ ፍጻሜ ውድድር ምሽት 2፡35 ሰዓት ላይ ይካሄዳል።
በውድድሩም አትሌት ጉዳፍ ጸጋዬ፣ ድርቤ ወልተጂ እና ብርቄ ኃየሎም ይሳተፋሉ።
አትሌት ጉዳፍ እና ድርቤ በቀጥታ ግማሽ ፍጻሜውን የተቀላቀሉ ሲኾን አትሌት ብርቄ ግን በድጋሚ ተወዳድራ ነው ለግማሽ ፍጻሜ የደረሰችው።
ኢትዮጵያ በፓሪሱ ኦሎምፒክ በሁለት የብር ሜዳሊያ 57ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!