ባሕር ዳር: ነሐሴ 2/2016 ዓ.ም (አሚኮ)በፓሪስ ኦሎምፒክ የወንዶች 3000 ሜትር መሰናክል የፍጻሜ ውድድር ትናንት ምሽት 4:43 ሰዓት ላይ መደረጉ ይታዎሳል።
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑክም ማጣሪያውን በጥሩ ብቃት ባለፉት አትሌት ለሜቻ ግርማ፣ አትሌት ጌትነት ዋለ እና አትሌት ሳሙኤል ፍሬው በርቀቱ ተወክሎ ነበር።
ነገር ግን የውድድሩ ተሳታፊ የነበረው አትሌት ለሜቻ ግርማ በመጨረሻዎቹ 200 ሜትር አካባቢዎች ላይ መሰናክሉን ለመዝለል ሲሞክር ክፉኛ በመውደቁ በቃሬዛ ከመሙ ላይ ተንስቶ ለሕክምና ተወስዷል።
ውድድሩን በስታዲየም ተገኝቶ የተከታተለው እና በቴሌቪዥን የተመለከተው የስፖርት ቤተሰብ በክስተቱ ድንጋጤ ተፈጥሮበታል። የጤና ሁኔታው “በምን ደረጃ ላይ ይኾን?” የሚለው ዜና ሲጠባበቅ ቆይቷል።
አትሌት ለሜቻ ግርማ በተደረገለት የጭንቅላት ሲቲ ስካን ምርመራ የራስ ቅሉ አለመጎዳቱ ተገልጿል። እግሩም በደህና ኹኔታ ላይ እንደሚገኝ ፍራንስ 24 ኒውስ የዓለም አሎምፒክ ኮሚቴን ጠቅሶ አስነብቧል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!