ባሕር ዳር: ነሐሴ 01/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በወንዶች የ3 ሺህ ሜትር መሰናክል ፍጻሜ ለሜቻ ግርማ፣ ጌትነት ዋለ እና ሳሙኤል ፍሬው ዛሬ ምሽት 4፡ 45 ላይ ይወዳደራሉ፡፡ በቶኪዮ በተካሄደው 32ኛው የኦሎምፒክ ጨዋታዎች በርቀቱ ያሸነፈው ሞሮኳዊው አትሌት ሶፊያን ኤል ባካሊ ለወርቅ ሜዳሊያው ከፍተኛ ግምት ተሰጥቶታል፡፡
ኢትዮጵያውያኑ ከሶፊያን ኤል ባካሊ በተጨማሪ ከዩጋንዳው ሊዮናርድ ቺሙታይ እና ከኬኒያው አሞስ ሴሬም የሚጠብቃቸው ፈተና ቀላል እንደማይኾን ይጠበቃል፡፡
ውድድሩን የማሸነፍ የቅድሚያ ግምት ከተሰጣቸው አትሌቶች መካከል አንዱ የኾነው ለሜቻ ከአንድ ዓመት በፊት በፈረንሳይ ፓሪስ በተካሄደው ዳይመንድ ሊግ 7 ደቂቃ ከ52 ሴኮንድ ከ11 ማይክሮ ሴኮንድ በመጨረስ የርቀቱን የዓለም ክብረ ወሰን አስመዝግቧል።
13ኛ ቀኑን በያዘው የኦሎምፒክ ጨዋታዎች ቀን 6፡ 10 ላይ በ5 ሺህ ሜትር ወንዶች የማጣሪያ ውድድር የሚኖር ሲኾን ቀን 7፡45 ላይ ደግሞ በሴቶች የ 1ሺህ 500 ሜትር የማጣሪያ ውድድር እንደሚካሄድ ከዓለማቀፉ የአትሌቲክስ ስፖርት የወጣው መርሐ ግብር ያሳያል፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!