ዩጋንዳዊ ጆሽዋ ቺፕቴጌ በ5 ሺህ ሜትር እንደማይወዳደር ታወቀ።

0
194

ባሕር ዳር: ሐምሌ 30/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ዩጋንዳዊ ጆሽዋ ቺፕቴጌ በ10 ሺህ ሜትር ከቀናት በፊት የወርቅ ሜዳልያ ባለቤት መኾኑ ይታወሳል። ቺፕቴጌ በ5 ሺህ ሜትርም ለወርቅ ቅድሚያ ካገኙ አትሌቶች መካከል ነበር። ነገር ግን ዩጋንዳዊው ጆሽዋ ቺፕቴጌ እና የቡድን አጋራ ጃኮብ ኪፕሊሞ ከፉክክሩ መውጣታቸውን ደይሊ ሞኒተር ዘግቧል።

ዩጋንዳዊ አልህ አስጨራሽ በነበረው የ10ሺ ሜትር ውድድር ከገጠማቸው ድካም ማገገም ባለመቻላቸው ነው ከ5ሺ ሜትር ውድድር ለመውጣት የተገደዱት።

በቶኪዮው ኦሊምፒክ የ5ሺህ ሜትር የወርቅ ሜዳሊያ ባለቤቱ ጆሽዋ ቺፕቴጌ ነበር። ዘንድሮ ደግሞ በ10ሺህ ሜትር ውድድር የቀነኒሳ በቀለን የኦሊምፒክ ክብረወሰን በመስበር ጭምር ማሸነፍ ችሏል።

ሁለቱ ዩጋንዳውያን አትሌቶች ከ10ሺ ሜትር ውድድር በኋላ እንዲያገግሙ በሐኪሞች እና ፊዚዮቴራፒ ባለሙያዎች ከፍተኛ ጥረት ቢደረግም እንዳልተሳካ የዩጋንዳ አትሌቲክስ አሠልጣኝ ፉስቲኖ ኪዋ በደብዳቤ ገልጸዋል።

ይህን ተከትሎ የኢትዮጵያ እና ኬንያ ሯጮች የተሻለ የማሸነፍ እድል አግኝተዋል። የ5ሺ ሜትር የማጣሪያ ውድድር ነገ፣ ፍጻሜው ደግሞ የፊታችን ቅዳሜ ይደረጋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here