በ2024ቱ የፓሪስ ኦሎምፒክ ቻይና የሜዳሊያ ሰንጠረዡን እየመራች ነው።

0
295

ባሕር ዳር: ሐምሌ 25/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የፓሪሱ ኦሎምፒክ ቀጥሏል። በኢትዮጵያውያን ዘንድ የሚወደደው የአትሌቲክስ ውድድር ተጀምሯል። ኢትዮጵያ ሜዳሊያ እንደምታስመዘግብባቸው ከሚጠብቁ ውድድሮች መካከል የወንዶች 10 ሺህ ሜትር ነገ ምሽት ይካሄዳል።

ከአትሌቲክስ ውጭ በሌሎች ውድድሮች ሀገራት ሜዳሊያዎችን እየሠበሠቡ ነው። ይህ ዜና አስከተሠራበት ሰዓት ድረስም ቻይና በርካታ ሜዳልያዎችን በማስመዝገብ በቀዳሚነት ተቀምጣለች። 11ወርቅ፣ 7 ብር እና 3 ነሀስ በድምሩ 21 እስካሁን ያሳካችው የሜዳልያ ብዛት ነው።

8 ወርቅ፣ 10 ብር፣ እና 8 ነሀስ የሠበሠበችው ፈረንሳይ ቻይናን እየተከተለች ነው። ጃፓን እና አውስትራሊያ ቀጣዮቹን ደረጃዎች በጊዚያዊነት ይዘዋል። የኦሎምፒክ ውድድሮችን በተደጋጋሚ በበላይነት በማጠናቀቅ ቀዳሚዋ አሜሪካ ለጊዜው አምስተኛ ደረጃ መቀመጣጧን የቢቢሲ መረጃ ያሳያል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here