እየተካሄደ ባለው የ2024ቱ ኦሎምፒክ በእግር ኳስ ሁለት የአፍሪካ ሀገራት ሩብ ፍጻሜ ደርሰዋል።

0
255

ባሕር ዳር: ሐምሌ 24/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በኦሎምፒክ ጨዋታዎች ሀገራት ሜዳልያ ውስጥ ለመግባት በተለያዩ ስፖርቶች ውድድርቸውን እያደረጉ ነው። በእግር ኳስ ከሚወዳደሩ ሀገራት መካከልም ለሩብ ፍጻሜ የበቁ ሀገራት ተለይተዋል። ከእነዚህ ሀገራት ውስጥም ሁለቱ አፍሪካውያን ናቸው።

የሞሮኮ እና ግብጽ የኦሎምፒክ ብሔራዊ ቡድኖች በውድድሩ ጥሩ ብቃት በማሳየት ሩብ ፍጻሜው ላይ ተገኝተዋል። አሜሪካ፣ ጃፓን፣ ፈረንሳይ፣ ስፔን፣ አርጀንቲና እና ፓራጓይ ሌሎች የሩብ ፍጻሜ ተጋጣሚ ሀገራት ናቸው።

ሞሮኮ ከአሜሪካ፣ ግብጽ ከፓራጓይ፣ ፈረንሳይ ከአርጀንቲና እና ጃፓን ከስፔን የግማሽ ፍጻሜ ቦታን ለመግኘት የሚደረጉ ጨዋታዎች መኾናቸውን የቢቢሲ መረጃ ያሳያል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here