“አትሌቶቹ በፓሪስ ኦሎምፒክ የዩክሬናውያንን የቀደመ ሰላማዊ ሕይዎት እንዲመለስ ለዓለም ሕዝብ ግንዛቤ ይፈጥራሉ” ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ

0
186

ባሕር ዳር: ሐምሌ 18/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ከሩሲያ ጋር በጦርነት ላይ የምትገኘው ዩክሬን አትሌቶቿን ወደ ፓሪስ ልካለች፡፡

የዩክሬኑ ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ “በኛ በዩክሬናውያን ላይ እየተካሄደ ያለው ጦርነት አትሌቶቻችንንም የሚመለከት ነው” ብለዋል። አትሌቶቹ በፓሪስ ኦሎምፒክ ተሳትፏቸው የዩክሬናዊያንን የቀደመ ሰላማዊ ሕይዎት እንዲመለስ ለዓለም ሕዝብ ግንዛቤ ይፈጥራሉም ነው ያሉት፡፡

የዩክሬን ብሔራዊ መዝሙር እና ሰንደቅ ዓላማ በፓሪስ ኦሎምፒክ ከሌሎች ሀገራት ጋር ብሔራዊ መዝሙር እና ሰንደቅ ዓላማ ከፍ ብሎ ይደመጣል፤ ይታያልም ያሉት ፕሬዚዳንቱ ይህ ደግሞ የኦሎምፒክ ተቀዳሚ ዓላማው ነውም ብለዋል፡፡ በፓሪስ ለሚሳተፉት ዩክሬናውያን አትሌቶች እና ይህንን ላመቻቹት አካላት ምሥጋናቸውን ያቀረቡት ዘለንስኪ ወደ ትላንት ሰላማዊ ሕይወታችን እንመለስ ዘንድ ሁሉም የዓለም ሕዝብ ያግዘን ሲሉም በቪዲዮ ባስተላለፉት መልእክት ጠይቀዋል፡፡

15 የሩሲያ አትሌቶች ብቻ በግላቸው በፓሪስ ኦሎምፒክ እንደሚሳተፉ የሮይተርስ ዘገባ ያመለክታል፡፡ ”ዓለም ሩሲያን መታገስ የለበትም“ ያሉት ዘለንስኪ ሩሲያ ከፓሪስ ኦሎምፒክ አትሌቶቿ በመገለላቸው የፑቲን እና ሕዝባቸው ስፖርታዊ ውድድር ዩክሬናውያንን መግደል እና ጦርነት ብቻ መኾኑን አሳይቷል ሲሉም ተደምጠዋል፡፡

ዘጋቢ፡- እሱባለው ይርጋ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here