የፓሪስ 2024 ኦሎምፒክ የኢትዮጵያ ልዑክ ፖሪስ ገባ።

0
330

ባሕር ዳር: ሐምሌ 18/2016 ዓ.ም (አሚኮ)የፓሪስ 2024 ኦሎምፒክ የመጀመሪያው ዙር የኢትዮጵያ ልዑክ ፖሪስ ገብቷል።

በፈረንሳይ መንግሥት ግብዣ በመክፈቻ ሥነ- ሥርዓት ላይ የሚገኙት ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ይገኙበታል። ቡድኑ በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር 2:30 ላይ ነው ፓሪስ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የደረሰው።

በዛሬው የመጀመሪያ ዙር ጉዞ ላይ የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ የሥራ አመራር ቦርድ፣ የተለያዩ ፌዴሬሽኖች መሪዎች፣ የክልሎች ቢሮ ኃላፊዎች፣ የውኃ ዋና ስፖርት ቡድን እና በተጠባባቂነት የተያዙት አትሌቶች ይገኙበታል።

ኢቢሲ እንደዘገበው ቀሪ የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ልዑክ በ5 ዙር ተከፋፍሎ ወደ ስፍራው እንደሚያቀናም ለማወቅ ተችሏል። የፓሪስ 2024 ኦሎምፒክ በነገው እለት ምሽት 2:30 ላይ በልዩ የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት በይፋ ይከፈታል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here