የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን የፓሪስ ኦሎምፒክን በድምቀት ለማስተናገድ በቂ ዝግጅት መደረጉን ተናገሩ።

0
294

ባሕር ዳር: ሐምሌ 17/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን የፓሪስ ኦሎምፒክ መንደርን ከጎበኙ በኋላ ”እንግዶቻችንን በበቂ ሁኔታ ለማስተናገድ ተዘጋጅተናል“ ብለዋል፡፡

ከመቶ ዓመት በፊት ኦሎምፒክን አስተናግዳ የነበረችው የፈረንሳይዋ ፓሪስ ከተማ የ 2024 ኦሎምፒክን እና የክረምቱን ፓራኦሎምፒክ ለማስተናገድ ዝግጅቷን አጠናቅቃለች፡፡ አርብ በ19/11/2016 ዓ.ም በሚጀመረው የፓሪስ ኦሎምፒክ 45 ሺህ የደኅንነት አባላት የፓሪስ ኦሎምፒክ ታዳሚዎችን፣ ጎብኚዎችን እና ሌሎችንም ደኅንነት ለመጠበቅ በተጠንቀቅ መቆማቸውን ፍራንስ 24 አስነብቧል፡፡

የፈረንሳይ አየር ኃይል በቀን 6 ሰው አልባ አውሮፕላኖችን (ድሮኖችን) ለ24 ሰዓታት በሰማይ ላይ በማሰማራት የከተማዋን ደኅንነት ያረጋግጣል፡፡ 30 ሺህ የፈረንሳይ ፖሊሶች በፓሪስ ጎዳናዎች እየተንቀሳቀሱ ሽብርተኞችን ለመከላከል፣ የሳይበር ጥቃቶች እንዳይፈጸሙ ለማድረግ እና ሌሎች የደኅንነት ሥጋቶች እንዳይኖሩ ለማድረግ ተዘጋጅተዋል፡፡

ፓሪስ ውበቷን ጥላሸት የሚቀባ አንዳችም ነገር እንዳይኖር ከሌሎች ከተሞቿ እና ከጎረቤት ሀገራት ሳይቀር የደኅንነት ባለሙያዎችን አሰማርታ እንደምትሠራ የፍራንስ 24 ዘገባ ይጠቁማል፡፡

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here