”ለፓሪስ ኦሎምፒክ የአትሌቶች ምርጫ ፈታኝ ነበር” የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት አሸብር ወልደጊዮርጊሥ (ዶ.ር)

0
252

ባሕር ዳር: ሐምሌ 03/2016 ዓ.ም (አሚኮ) አብዛኞቹ ዕጩ አትሌቶች ተቀራራቢ ሰዓት እንደነበራቸው የገለጹት ፕሬዚዳንቱ የመጨረሻ የተመረጡ አትሌቶች ባላቸው ሰዓት ተመርጠው ለዓለም አቀፉ ኦሎምፒክ ኮሚቴ መላኩን አብራርተዋል።

ዶክተር አሸብር ወልደጊዮርጊስ “በዚህ ምርጫ ልባቸው ለተሰበረ አትሌቶች ይቅርታ መጠየቅ እንፈልጋለን፤ በዚህም አትሌቶች ተስፋ መቁረጥ የለባቸውም” ብለዋል።

የአትሌት ጉዳፍ ፀጋዬ በ3 ርቀት መሳተፍን በተመለከተ ለቀረበላቸው ጥያቄም ”ያላት ሰዓት ነው እንድትመረጥ ያደረጋት፤ ይህ ማለት ግን በሦስቱም ርቀቶች ትሳተፋለች ማለት አይደለም” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

ከፍሬወይኒ ሀይሉ ቅሬታ ጋር በተገናኘም ተጠባባቂ ማለት አይወዳደርም ማለት አይደለም ብለዋል። በተጠባባቂነት ከተያዘችባቸው ሁለት ርቀቶች በአንዱ ልትሮጥ እንደምትችልም ፍንጭ ሰጥተዋል ሲል ኢቢሲ መረጃውን አጋርቷል፡፡

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here