በደሴ ከተማ “ሰላም ለሁሉም፤ ሁሉም ለሰላም” በሚል መሪ ቃል የ5 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ የሩጫ ውድድር ተካሄደ።

0
200
ባሕር ዳር፡ ሰኔ 30/2016 ዓ.ም (አሚኮ) “ሰላም ለሁሉም ሁሉም ለሰላም” በሚል መሪ ቃል የጎዳና ላይ የሩጫ ዉድድር በዛሬው ዕለት በድምቀት ተደርጓል።
በሩጫ ዉድድሩ ላይ የአማራ ክልል ወጣትና ስፖርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ ጋሻዉ ተቀባ፣ አቶ አዱኛ ይግዛው የአማራ ክልል ወጣትና ስፖርት ቢሮ አማካሪ፣ ሌሎች የክልል አመራሮች፣ የደሴ ከተማ የከተማ አመራሮች እንዲሁም የስፖርት ቤተሰቦች ተሳትፈዋል። ዉድድሩ ስፖርትን ለሰላም በመጠቀም ዜጎች ለሰላም ዘብ እንዲቆሙ ለማስቻልና የጎዳና ላይ ሩጫ ዉድድሩ ሰላምን የበለጠ ለማፅናትና አንድነትን ለማጠናከር ትልቅ ፋይዳ የሚጫወት በመሆኑና የሕዝብን አብሮነት፣ ወንድማማችነትንና እህትማማችነትን ለማጎልበት ታልሞ የተዘጋጀ መሆኑ ተገልጿል።
የደሴ ከተማ ኮሙኒኬሽን መረጃ እንደሚያሳየው ውድድሩን በአሸናፊነት ላጠናቀቁ ተወዳዳሪዎች የዋንጫ፣ የሜዳሊያና የገንዘብ ሽልማት ከዕለቱ የክብር እንግዶች ተበርክቶላቸዉ መርሐ ግብሩ በድምቀት ተጠናቋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here