በፓሪስ ኦሎምፒክ ኢትዮጵያን የሚወክሉ የመጨረሻ አትሌቶች ታውቀዋል፡፡

0
240

ባሕር ዳር: ሰኔ 28/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በፓሪሱ 2024 ኦሊምፒክ ጨዋታዎች በአትሌቲክስ ስፖርት ኢትዮጵያን የሚወክሉ የመጨረሻ ተሰላፊ አትሌቶች ከነተጠባባቂያቸው መታወቃቸውን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አስታውቋል።
በዚህም መሠረት ፡-

800 ሜትር ሴቶች ፅጌ ድጉማ፣ ሐብታም ዓለሙ እና ወርቅነሽ መለሰ ሲመረጡ ንግስት ጌታቸው ተጠባባቂ ኾናለች።

1ሺህ 500 ሜትር ወንዶች አብዲሳ ፈይሳ፣ ሳሙኤል ተፈራ፣ ኤርሚያስ ግርማ በቀዳሚነት ታደሰ ለሚ በተጠባባቂነት ተመርጠዋል።

1ሺህ 500 ሜትር ሴቶች ጉዳፍ ፀጋዬ፣ ብርቄ ሃየሎም እና ድርቤ ወልተጂ የተመረጡ ሲኾን ሂሩት መሸሻ ተጠባባቂ ኾናለች።

5ሺህ ሜትር ወንዶች ሀጎስ ገ/ህይወት፣ ዮሚፍ ቀጄልቻ እና አዲሱ ይሁኔ በዋናነት ሰለሞን ባረጋ ደግሞ በተጠባባቂነት ተመርጠዋል።

በ5ሺህ ሜትር ሴቶች ጉዳፍ ፀጋዬ፣ መዲና ኢሳ እና እጅጋየሁ ታዬ በቀዳሚነት ሲመረጡ ተጠባባቂዋ ፍሬወይኒ ኃይሉ ኾናለች።

10 ሺህ ሜትር ወንዶች ዮሚፍ ቀጄልቻ፣ በሪሁ አረጋዊ እና ሰለሞን በረጋ ናቸው የተመረጡት። ቢኒያም መሀሪ ደግሞ ተጠባባቂ ኾኗል።

10 ሺህ ሜትር ሴቶች ጉዳፍ ፀጋዬ፣ ፎቴን ተስፋዬ እና ፅጌ ገ/ሰላማ ተመርጠዋል። አይናዲስ መብራቱ ተጠባባቂያቸው ናት።

በ3 ሺህ ሜትር መሠናክል ወንዶች ለሜቻ ግርማ፣ ሳሙኤል ፍሬው እና ጌትነት ዋለተሠራጭ ኾነዋል። አብርሃም ስሜ ደግሞ የርቀቱ ተጠባባቂ ነው።

3ሺህ ሜትር ሴቶች ሲምቦ ዓለማየሁ እና ሎሚ ሙለታ በፓሪስ ሀገራቸውን ይወክላሉ።

በማራቶን ሴቶች ትዕግስት አሰፋ፣ አማኔ በሪሶ እና መገርቱ ዓለሙ እንዲሁም ጎይቶቶም ገ/ስላሴ ተጠባባቂ በመኾን ተመርጠዋል።

በማራቶን ወንዶች ቀነኒሳ በቀለ፣ ሲሳይ ለማ እና ዴሬሳ ገለታ በቀዳሚነት ታምራት ቶላ ደግሞ በተጠባባቂነት ተመርገዋል።

20 ኪሎ ሜትር ርምጃ በወንድ ምስጋና ዋቁማ እንዲሁ ሀገሩን እንደሚወክል ታውቋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here