በኮፓ አሜሪካ ዋንጫ አርጀንቲና ግማሽ ፍጻሜ ደርሳለች።

0
319

ባሕር ዳር: ሰኔ 28/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የኮፓ አሜሪካ ዋንጫ በአሜሪካ አስተናጋጅነት እየተካሄደ ነው። የሩብ ፍጻሜ ጨዋታዎች መካሄድ ጀምረዋል። ትናንት ሌሊት ኢኳዶርን የገጠመችው አርጀንቲና በፈተና ተንገላታም ቢኾን የግማሽ ፍጻሜ ቦታዋን አረጋግጣለች። ጨዋታው አንድ እኩል ነው የተጠናቀቀው።

ነገር ግን አርጀንቲና በመለያ ምት 4 ለ 2 በማሸነፍ ወደ ቀጣዩ ዙር አልፋለች። በረኛው ኢሚላኖ ማርቲኔዝ ሁለት ኳሶችን በማዳን አርጀንቲናን ታድጓል። በአንጻሩ ሊዮኔል መሲ የመለያ ምት ስቷል።

የኮፓ አሜሪካው ጨዋታዎች ሲቀጥሉ ዛሬ ሌሊት ቬንዜውላ ከካናዳ፣ ቅዳሜ ኮሎምቢያ ከፓናማ ይጫወታሉ። ተጠባቂው የብራዚል እና ኡራጋይ ጨዋታ ደግሞ እሁድ ሌሊት ይካሄዳል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here