በአፍሪካ ክለቦች የጠረጴዛ ኳስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ የነሐስ ሜዳሊያ አገኘች፡፡

0
183

ባሕር ዳር: ሰኔ 21/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የጠረጴዛ ኳስ ቡድን በሊቢያ ቤንጋዚ በተካሄደው የአፍሪካ ክለቦች ሻምፒዮና ተሳትፎ የነሐስ ሜዳሊያ አሸናፊ መኾን ችሏል፡፡

ከሰኔ 20/2016 ዓ.ም እስከ ሰኔ 21/2016 ዓ.ም በሊቢያ አዘጋጅነት ሲካሄድ በቆየው የአፍሪካ የጠረጴዛ ኳስ ክለቦች ሻምፒዮና ኢትዮጵያን ወክሎ የተሳተፈው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የጠረጴዛ ኳስ ቡድን በሴቶችም በወንዶችም ነው የነሐስ ሜዳሊያ በማግኘት ውድድሩን ያጠናቀቀው፡፡

የምሥራቅ አፍሪካ ብቸኛ ተወካይ የኾነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የጠረጴዛ ኳስ ቡድን በሻምፒዮናው ከተሳተፉት የሊቢያ፣ ግብጽ፣ ናይጄሪያ እና ቱኒዚያ ቡድኖች ጋር ተወዳድሮ ያገኘው ውጤት የሚያኮራ እንደኾነ ነው የተገለጸው፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ እንዳለው በተገኘው ውጤት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የጠረጴዛ ኳስ ቡድን ባለፉት አራት ዓመታት ተመዝግቦ ከነበረው የሜዳሊያ ሠንጠረዥ ውስጥ በመግባት ታሪክ መሥራት ችሏል፡፡

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here