ዛሬ የተሰሙ የዝውውር ወሬዎች

0
338

ባሕርዳር: ታኅሳሥ 29/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የፈረንሣይ ብሔራዊ ቡድንና የፓሪስ ሴንት ዠርሜይን አጥቂ ኪሊያን ምባፔ በኮንትራቱ መጨረሻ ሪያል ማድሪድን ለመቀላቀል መስማማቱን ቢቢሲ አስነብቧል።

ምባፔ ከፓሪስ ሴንት ዠርሜ ቡድን ጋር ያለው ስምምነት በቀጣይ ሰኔ ይጠናቀቃል ነው የተባለው።

ባርሴሎና የቀድሞውን የማንቸስተር ዩናይትድ አማካይ እንግሊዛዊውን ጄሴ ሊንጋርድን ለማስፈረም እየተዘጋጀ መኾኑንም ተነግሯል።

ጁቬንቱስ ከ25 ዓመቱ አማካኝ ዌስተን ማኬኒ ጋር የኮንትራት ማራዘሚያ ንግግር ለማድረግ ተዘጋጅቻለሁ ማለቱን “ጎል” በድረ ገጹ አስነብቧል፡፡

የአርሰናሉ አሠልጣኝ ሚኬል አርቴታ ቡድናቸው በዚህ የተጫዋቾች የዝውውር ወቅት የተሻሉ አጥቂዎችን ለማስፈረም ያደረገው ጥረት አልተሳካም ማለታቸውን ስካይ ስፖርት ዘግቧል፡፡

እንግሊዛዊ የኒውካስትል አማካይ ሴን ሎንግስታፍ ትክክለኛ ጥያቄ የሚያቀርብለት ቡድን ካገኘ ክለቡን ለመልቀቅ መወሰኑን ሰን አስነብቧል፡፡

ቶተንሃም የ21 ዓመቱን ሩማኒያዊ ተከላካይ ራዱ ድራጉሲን ከጅኖዋ ላይ በሳምንቱ መጨረሻ አካባቢ ለማስፈረም ተስፋ አድርገዋል መባሉን ዴይሊ ሜይል ዘግቧል፡፡

በሙሉጌታ ሙጨ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here