ጣሊያን እና ስፔን የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል።

0
181

ባሕር ዳር: ሰኔ 13/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በአውሮፓ ዋንጫ የምድብ ጨዋታዎች ጣሊያን እና ስፔን ይጫወታሉ። ሁለቱ ቡድኖች የመጀመሪያ የምድብ ጨዋታቸውን አሸንፈው ነው ዛሬ የሚገናኙት። ስፔን ክሮሽያን፣ ጣሊያን ደግሞ አልባንያን ማሸነፋቸው ይታወሳል።

በሌላ ጨዋታ እንግሊዝ ዴንማርክን የምትገጥምበት ጨዋታም ትኩረት ስቧል። እንግሊዝ የመጀመሪያ የምድብ ጨዋታው ሰርቪያን በማሸነፍ በድል መጀመሯ ይታወሳል። ዴንማርክ በበኩሏ ከስሎቪኒያ ጋር ነጥብ ተጋርታለች።

በዚሁ ምድብ ስሎቪኒያ ከሰርቪያ የሚያደርጉት ጨዋታም በውድድሩ የመቆየት ተስፋን ከፍ ለማድረግ የሚደረግ የምት ሽረት ጨዋታ ነው።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here