በመጀመሪያ የምድብ ጨዋታዎች በየጨዋታው ኮከብ የተባሉ ተጫዋቾች።

0
213

ባሕር ዳር: ሰኔ 12/2016 ዓ.ም (አሚኮ) 17ኛው የአውሮፓ ዋንጫ በጀርመን እየካሄደ ነው። በመጀመሪያው ዙር በየጨዋታው ምርጥ ብቃታቸውን ያሳዩ ተጨዋቾችም ተሸልመዋል፡፡ በመክፈቻው ጨዋታ ጀርመን ስኮትላንድን 5 ለ 1 ባሸነፈችበት ጨዋታ ጀማል ሙሲያላ የጨዋታው ኮከብ ተብሎ ተሸልሟል፡፡

ሀንጋሪ ከስዊዘርላንድ ባደረጉት ጨዋታ ላይ ደግሞ ስዊዘርላንድ ሀንጋሪን 2 ለ 1 ረትታለች፡፡ የጨዋታው ኮኮብም የስዊዘርላንዱ አምበል ግራኒት ዣካ ኾኗል፡፡ ስፔን ክሮሺያን 3 ለ 0 ባሸነፈችበት ጨዋታ ስፔናዊው አማካይ ፋቢያን ሩዝ የጨዋታው ኮከብ ተብሏል፡፡ ጣሊያን አልባኒያን ተቸግራ 2 ለ 1 ስታሸንፍ ፌዴሪኮ ኬዛ የጨዋታው ኮከብ ኾኖ ተመርጧል፡፡

ፖላንድ በኔዘርላንድ 2 ለ 1 በተሸነፈችበት ጨዋታ የጨዋታው ኮከብ ተብሎ የተመረጠው የሊቨርፑሉ ኮዲ ጋክፖ ነው፡፡ ስሎቬኪያ እና ዴኒማርክ 1 ለ1 በተለያዩበት ጨዋታ የዴኒማርኩ ክርስቲያን ኤሪክሰን የጨዋታው ኮከብ የሚል ክብርን አግኝቷል፡፡ ሰርቢያ በኢንግላንድ 1 ለ 0 ስትሸነፍ፣ የማሸነፊያ ግቧን ያስቆጠረው እንግሊዛዊው ጁዲ ቤሊንግሀም የጨዋታው ኮከብ ኾኗል፡፡

ሮማኒያ ዩክሬንን 3 ለ 0 በኾነ ሰፊ ውጤት ስታሸንፍ የሮማኒያው አምበል ኒኮላይ ስታንቹ የጨዋታው ምርጥ ተብሏል፡፡ ቤልጅየም በስሎቫኪያ ባልተጠበቀ ኹኔታ 1 ለ 0 ስትሸነፍ ለስሎቫኪያ ግቧን ያስቆጠረው ኢቫን ቫራንዝ የጨዋታው ኮከብ የመኾን ዕድልንም አግኝቷል፡፡ ፈረንሳይ ብዙ ተፈትና ኦስትሪያን 1 ለ 0 ባሸነፈችበት ጨዋታ የመሀል ሜዳው ሞተሩ ኒጎሎ ካንቴ የጨዋታውን ምርጥነት ክብርን አግኝቶበታል፡፡

ተርኪየ ጆርጂያን 3 ለ 1 በረታችበት ጨዋታ ደግሞ ወጣቱ የተረኪየ ባለ ተስፋ አርዳ ጉለር የጨዋታው ኮከብ ኾኖበታል፡፡ ፖርቹጋል ከቼክ ሪፐብሊክ ጋር ባደረገችው እልህ አስጨራሽ ጨዋታም ፖርቹጋላዊው ቪቲኒሃ የጨዋታ ኮከብነትን ማዕረግ ማግኘቱን ኢስፒኤን ጽፏል። ዛሬ የሚጀመረው የየምድቦቹ ሁለተኛ ጨዋታ እነማንን በኮከብ ተጨዋችነት እየሰየመ እና እየሸለመ እንደሚሄድ በቀጣይ እንመለከታለን፡፡

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here