ባሕር ዳር: ሰኔ 12/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በካሜሮን ዱዋላ ከተማ በሚደረገው በ23ኛው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ የሚካፈለው የኢትዮጵያ ልዑክ በዛሬው እለት ከጠዋቱ ሰዓት ላይ ወደ ካሜሮኗ ዱዋላ አቅንቷል ። የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ምክትል ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ማስተዋል ዋለልኝ በቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ በመገኘት ቡድኑን ሸኝተዋል ።
የአትሌቲክስ ፌዴሬሽኑ ለልዑካን ቡድኑ መልካም ቆይታ እና ውጤት መመኘቱንም የአትሌቲክስ ፌዴሬሽኑ በማኅበራዊ የትሥሥር ገጹ አስነብቧል፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!