ባሕር ዳር: ሰኔ 11/2016 ዓ.ም (አሚኮ)የፖርቹጋል ብሔራዊ ቡድን የተከላካይ መስመር ተጫዋች ፔፔ እና የፊት መስመር ተጫዋቹ ሮናልዶ አዲስ ታሪክ አስመዝግበዋል። የፖርቹጋል ብሔራዊ ቡድን ከቼክ ሪፐብሊክ ብሔራዊ ቡድን ጋር ያደረገውን የአውሮፓ ዋንጫ የምድብ የመጀመሪያ ጨዋታ 2 ለ 1 በኾነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።
ለፖርቹጋል ብሔራዊ ቡድን የማሸነፊያ ግቦችን ፍራንሴስኮ ኮንሴካኦ እና ፕሮቮድ በራሱ ግብ ላይ ሲያስቆጥሩ ለቼክ ህራናክ አስቆጥሯል። ፖርቹጋላዊው ተከላካይ ፔፔ በአውሮፓ ዋንጫ ውድድር የተሳተፈ በእድሜ ትልቁ ተጨዋች በመኾን አዲስ ታሪክ መፃፍ ችሏል። የአምስት ጊዜ የባሎንዶር አሸናፊው እና የፖርቹጋል ብሔራዊ ቡድን አምበል ክርስቲያኖ ሮናልዶ በስድስት የአውሮፓ ዋንጫ ውድድሮች በመሳተፍ በውድድሩ ታሪክ ቀዳሚው ተጨዋች መኾን ችሏል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!