የቤልጀም ወርቃማ ትውልድ መጨረሻ?!

0
268

ባሕር ዳር: ሰኔ 11/2016 ዓ.ም (አሚኮ)

ቤልጅየም ፊፋ በሚያወጣው የደረጃ ሰንጠረዥ በአርጀንቲና እና በፈረንሳይ ብቻ ተቀድማ በሦስተኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠች ሀገር ናት፡፡ በ17ኛው የአውሮፓ ዋንጫ ቤልጅየምን 1ለ0 ያሸነፈችው ስሎቫኪያ ደግሞ በፊፋ የደረጃ ሰንጠረዥ 48ኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች፡፡ ወርቃማው የቤልጅየም ትውልድ እየተባለ የሚጠራው የእነ ሀዛርድ፣ ዲብሮይን፣ ሉካኩ፣ ኮርቱዋ እና የመሳሰሉ ኮከቦች ሥብስብ ለብሔራዊ ቡድናቸው ያስመዘገቡት ውጤት በተጠበቀው ልክ አይደለም።

ቤልጀም ትላንት ምሽት በአውሮፓ ዋንጫ በስሎቫኪያ መሸነፏም እያነጋገረ ነው ።ኢቫንዝ ቫራንዝ ያስቆጠራት ብቸኛ ግብ ቤልጅየማውያንን አንገት ስታስደፋ ስሎቫኪያውያን በአውሮፓ ዋንጫ ታሪካቸው አስደሳቹን ውጤት እንዲያስመዘግቡ አግዟል። ቤልጅየም በአሠልጣኝ ዶሚኒኮ ቴዴስኮ መሠልጠን ከጀመረች ከ16 ጨዋታ በኋላ ነው በስሎቫኪያ ሽንፈትን እያስተናገደች። የቴሌግራፍ ዘገባ እግር ኳስን ተወዳጅ ከሚያደርጉት ነገሮች አንዱም የዚህ ዓይነቱ ያልተገመተ ውጤት መኾኑን ጠቅሷል፡፡

የቤልጅየም አጥቂ ሮሚዮ ሉካኩ በስሎቫኪያ መረብ ላይ ሁለት ግቦችን ቢያሳርፍም አንዱ ከጨዋታ ውጪ እና አንዱ ደግሞ በእጅ የተነካ ነው በሚል በዳኛው ተሽሯል፡፡ በምድብ አምስት ቤልጅየም፣ ሮማኒያ እና ዩክሬን ጋር የተደለደለችው ስሎቫኪያ በምድቧ ዩክሬንን 3 ለ 0 ካሸነፈችው ሮማኒያ ቀጥላ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች፡፡

የቤልጅየም ወርቃማው ትውልድ ቀሪ ተስፋ የዘንድሮው የአውሮፓ ዋንጫ ነው። በቀጣይ በውድድሩ የሚያሳየው ብቃትም ይጠበቃል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here