ባሕር ዳር: ሰኔ 11/2016 ዓ.ም (አሚኮ)
ቢቢሲ ባጋራው መረጃ መሰረት ብዙ ተመልካቾች ያለው የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ አርብ ነሐሴ 10/2016 ዓ.ም ይጀምራል። ፕሪምየር ሊጉም የኤፍ ኤ ዋንጫ አሸናፊው ማንቸስተር ዩናይትድ ከፉልሃም በሚገናኙበት ጨዋታ ይከፈታል። አዲስ አዳጊው ኤስፒች ታውንን ከሊቨርፑል ጋር የሚያፋልመው የፕሪሚየር ሊጉ የመጀመሪያ ሳምንት ጨዋታ፣ ቼልሲ በስታምፎርድ ብሪጅ ሻምፒዮናውን ማንቸስተር ሲቲን የሚጋብዝበት ጨዋታም ከተጠባቂ የመጀመሪያ ሳምንት መርሐ ግብሮች ውስጥ ይጠቀሳሉ።
ሌሎች የፕሪምየርሊጉ የመጀመሪያ ሳምንት መርሐግብሮች :-
ቅዳሜ ነሐሴ 11/2016 ዓ.ም
አርሴናል ከ ዎልቭስ
ኤቨርተን ከ ብራይተን
ኒውካስትል ከ ሳውዝአምፕተን
ኖቲንግሃም ከ በርንማውዝ በተመሳሳይ 11:00ሰ ይካሄዳሉ።
ዌስትሃም ከ አስቶንቪላ ደግሞ 1፡30 ላይ የሚካሄድ ይሆናል።
እሁድ ነሐሴ 12/2016 ዓ.ም
ብሬንትፎርድ ከ ክሪስታል.ፓ 10፡00 ሰዓት የዓመቱ የመጀመሪያ ታላቅ ጨዋታ
ቼልሲ ከማንቸስተር ሲቲ 12፡30 ላይይጫወታሉ።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!