ባሕር ዳር: ሰኔ 11/2016 ዓ.ም (አሚኮ)
ፈረንሳዊ አጥቂ ኪሊያን ምባፔ ትናንት ከኦስትሪያ ጋር በነበረው ጨዋታ የአፍንጫ ጉዳት አጋጥሞታል። የፈረንሳይ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የተጫዋቹን ጉዳት አስመልክቶ ባወጣው መረጃ አጥቂው የአፍንጫ ስብራት አግጥሞታል።
ህክምና እንደሚደረግለት የገለጸው ፌዴሬሽኑ ቆዶ ህክምና ግን በቅርቡ አያከናውንም ብሏል። በተጨማሪም በቀጣይ ጨዋታዎች ምባፔ ማስክ/መከላከያ/ በማድረግ አንደሚጫወት ተገልጿል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!