በአውሮፓ ዋንጫ ፈረንሳይ ኦስትሪያን አሸነፈች።

0
198

ባሕር ዳር: ሰኔ 10/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በዱሰልዶርፍ አሬና ስታዲየም ምሽት 4 ሰዓት ላይ በተደረገ የምድብ 4 ጨዋታ ፈረንሳይ ኦስትሪያን 1 ለ 0 አሸንፋለች፡፡

ኦስትሪያዊው ማክሲሚሊያን ዎበር በራሱ መረብ ላይ ባስቆጥራት ግብ ነው ፈረንሳይ አሸናፊ የኾነችው። በዚህ ጨዋታ ድንቅ ብቃት ያሳየው ንጎሎ ካንቴ የጨዋታው ኮከብ ኾኖ ተመርጧል። በአውሮፓ ዋንጫ ግብ አስቆጥሮ የማያውቀው የእግርኳስ ኮከቡ አዲሱ የሎስ ብላንኮዎቹ ማድሪዶች ፈራሚ ኪሊያን ምባፔ ሀገሩ ዛሬ አሸናፊ ብትሆንም እሱ ግን ግብ ማስቆጠር አልቻለም።

በአውሮፓ ዋንጫ ከዚሁ ምድብ ትናንት በተደረገ ጨዋታ ኔዘርላንድስ ፖላንድን 2 ለ 1 ማሸነፏ የሚታወስ ነው፡፡በሌላ ጨዋታ ምሽት 1 ሰዓት ላይ ቤልጂየም በስሎቫኪያ የ1 ለ 0 ያልተጠበቀ ሽንፈት አስተናግዳለች፡፡ ቀን 10 ሰዓት በተደረገ ሌላ ጨዋታ ደግሞ ሮማንያ ዩክሬንን 3 ለ 0 መርታቷ የሚታወስ ነው።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here