“የባንጃ ቮሊቦል ቡድን ያስመዘገበው ውጤት የአማራ የክልልን የቮሊቦል ስፖርት የሚያነቃቃ ነው” የአማራ ክልል ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ

0
304

ባሕር ዳር: ሰኔ 05/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ ቮሊቦል ክለቦች አሸናፊ የኾነው ባንጃ ቮሊቦል ክለብ በአማራ ክልል ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ደማቅ አቀባበል ተደረገለት። በአቀባበል ሥርዓቱ ላይ የተገኙት የአማራ ክልል ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ምክትል ኅላፊ ጋሻው ተቀባ የባንጃ ቮሊቦል ቡድን ያስመዘገበው ውጤት እጅግ የሚያስደስት እና በቀጣይ የክልሉን የቮሊቦል ስፖርት ለማነቃቃት የሚረዳ ነው ብለዋል።

ስፖርት ለሰላም፣ ሰላምም ለስፖርት አስፈላጊ በመኾናቸው ስፖርተኞች እና አሠልጣኞች ለሰላም መጎልበት የበኩላቸውን ሊወጡ እንደሚገባ ምክትል ኅላፊው ተናግረዋል። በአማራ ክልል ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ በተደረገላቸው አቀባበል ደስተኛ እንደኾኑ እና ለቀጣይ ዝግጅታቸው ትልቅ ማበረታቻ እንደሚኾናቸው የቡድኑ መሪዎች እና ስፖርተኞች ገልጸዋል።

የባንጃ ቮሊቦል ቡድን በ2017 ዓ.ም የአማራ ክልልን በመወከል በኢትዮጵያ ቮሊቦል ፕሪምየር ሊግ ተሳታፊ መኾኑን አረጋግጧል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here