በሴካፋ ካጋሜ ዋንጫ በዛንዚባር ሊካሄድ ነው፡፡

0
271

ባሕር ዳር: ሰኔ 04/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በ13 ክለቦች መካከል እንደሚደረግ የሚጠበቀው የሴካፋ ካጋሜ ዋንጫ ውድድር ላይ የሚሳተፉ ክለቦች ታውቀዋል፡፡ የውድድሩ ቀንም ማሻሻያ ተደርጎበታል። የምሥራቅ እና መካከለኛው የአፍሪካ ሀገራትን ያቀፈው ሴካፋ የቀጣናውን የተለያዩ የብሔራዊ ቡድኖች ውድድር ከማዘጋጀቱ በተጨማሪ እንደ ሴካፋ ካጋሜ ካፕ ያሉ የክለቦችን ውድድርም እንደሚያደርግ ይታወቃል።

ባለፈው ሁለት ዓመት ያልተከናወነው ይህ የሴካፋ የክለቦች ሻምፒዮና ውድድር ቀድሞ ከተያዘለት ጊዜ የቀን ማሻሻያ ተደርጎበታል። በመኾኑም ከሰኔ 29/2016 ዓ.ም እስከ ሐምሌ 15/2016 ዓ.ም ድረስ በታንዛኒያ እና ዛንዚባር ይከናወናል።

ሴካፋ ይፋ ባደረገው የውድድሩ ተሳታፊ ሀገራት ዝርዝር ላይ ኢትዮጵያዊ የኾነ ክለብ አለመኖሩን ሶከር ኢትዮጵያ አስነብቧል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here