የፉልሀሙ ተከላካይ ቶሲን አዳራቢዮን ክለቡ ያቀረበለትን ከፍተኛ ክፍያ በመተው ወደ ቼልሲ ተዘዋወረ።

0
268

ባሕር ዳር: ግንቦት 30/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ቼልሲ የፉልሀሙን ተከላካይ ቶሲን አዳራቢዮን በነፃ ዝውውር በአራት ዓመት ኮንትራት ማስፈረሙ ተረጋግጧል፡፡ የቀድሞው የማንቸስተር ሲቲ አካዳሚ ተመራቂ አዳራቢዮ በፉልሃም ከፍተኛ ገንዘብ እንደሚከፈለው የቀረበለትን ጥያቄ ውድቅ በማድረግ ነው ለቼልሲ የፈረመው፡፡

ተጫዋቹ በ2023/24 የውድድር ዘመን በፕሪሚየር ሊጉ ለፉልሃም 20 ጨዋታዎችን አድርጎ ሁለት ግቦችን አስቆጥሯል፡፡ የ26 ዓመቱ የመሐል ተከላካዩ አዳራቢዮን በፊርማ ሥነ ሥርዓቱ ላይ “የተወለድኩት ከስታምፎርድ ብሪጅ በቅርብ ርቀት ላይ በመኾኑ በሜዳው ጨዋታዎችን አድርጌያለሁ፡፡ እናም ይህን ትልቅ ቡድን በመቀላቀሌ በጣም ተደስቻለሁ ፡፡ በአቅሜ ለማገዝም በትጋት እሠራለሁ ” በማለት መናገሩን ሮይተርስ አስነብቧል፡፡

ተጫዋቹ እንደ አውሮፓ አቆጣጠር ከ2012 ጀምሮ እስከ 2015 ለእንግሊዝ ወጣት ብሔራዊ ቡድን በ14 ጨዋታዎች ላይ ተሰልፎ የተጫወተው አዳራቢዮ በቡድን ደረጃ ደግሞ ለዌስት ብሮምዊች አልቢዮን፣ ለብላክበርን ሮቨርስ እና ለፉልሀም 182 ጨዋታዎች ተሰልፎ ስምንት ግቦችንም ማስቆጠር ችሏል፡፡

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here