በሰሜን አሜሪካ የአትሌቶች ማኀበር ኢትዮጵያ በምትፈልጋቸው ወቅት ሁሉ አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መኾናቸውን ገልጹ።

0
209

ባሕር ዳር: ግንቦት 30/2016 ዓ.ም (አሚኮ)

በሰሜን አሜሪካ የአትሌቶች ማኀበር አባላት ለ“ጽዱ ጎዳና ኑሮ በጤና” 8 ሺህ 300 የአሜሪካን ዶላር የገንዘብ ድጋፍ አድርገዋል። በተጨማሪም አንድ መጸዳጃ ቤት በመሥራት የአይነት ድጋፍ የማድረግ ፍላጎት እንዳላቸው ገልጸዋል። ይኽን ድጋፋቸውን በአሜሪካ የኢትየጵያ ልዩ መልእክተኛ እና ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ስለሺ በቀለ አስረክበዋል።

የማኀበሩ ምክትል ፕሬዝዳንት አትሌት ሃይሉ መኮንን ኢትዮጵያ በምትፈልጋቸው ወቅት ሁሉ አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መኾናቸውን ገልጸዋል። አምባሳደር ስለሺ በቀለ የማኀበሩ አባላት በተለያዩ ሀገራዊ ጥሪዎች ላይ ያበረከቱት አስተዋጽኦ ከፍተኛ መኾኑን ጠቅሰው አኹንም ማኀበሩ ለ”ጽዱ ጎዳና ኑሮ በጤና” ኢንሼቲቭ ላደረገው ድጋፍ ያላቸውን ምስጋና አቅርበዋል።

በአሜሪካ ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና ትውልድ ኢትዮጵያውያን ለ”ጽዱ ጎዳና ኑሮ በጤና” እስከ አኹን በአጠቃላይ በጥሬ ገንዘብ 29 ሺህ 445 የአሜሪካ ዶላር እንዲኹም 74 ሺህ የኢትዮጵያ ብር ተሰብስቧል። በአይነት 21 ሚሊዮን ብር የሚገመቱ 14 መጸዳጃ ቤቶችን ለመሥራት ቃል መግባታቸውን በአሜሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመለክታል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here