ቫር እንዲቀጥል ተወሰነ።

0
192

ባሕር ዳር: ግንቦት 29/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ከፍተኛ ትችት እና ወቀሳ እየቀረበበት የሚገኘው የቪዲዮ ረዳት ዳኝነት (ቫር) አሠራር እንዲቀጥል ድምጽ መሰጠቱ ተነገረ።

የእንግሊዙ ወልቭስ ቡድን በዋነኛነት የቫር አሠራር እንዲነሳ የሚል ይፋዊ ጥያቄ አቅርቦ እንደነበር ስካይ ስፖርት አስታውሷል። በዚህም መሠረት ዛሬ አሠራሩ እንዲቀር ወይም እንዲቀጥል በፕሪሚየር ሊጉ ቡድኖች በተሰጠ ድምፅ 19 ለ 1 በኾነ ድጋፍ በቀጣዩ የውድድር ዘመን አሠራሩ እንዲቀጥል ተወስኗል።

በወልቭስ አሠራሩ እንዲቀር የሚጠይቀው ሃሳብ ለመጽደቅ ቢያንስ በ14 ቡድኖች መደገፍ ነበረበት።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here