ፌዴሬሽኑ ወልቂጤ ከተማ ላይ አስተማሪ የኾነ እርምጃን እንደሚወስድ አስታወቀ።

0
269

ባሕር ዳር: ግንቦት 28/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ወልቂጤ ከተማ ተጫዋቾቹ የጠየቁትን ካልፈጸመ ለሌሎች ክለቦች አስተማሪ የኾነ ቅጣትን አስተላልፋለሁ ብሏል። ፌዴሬሽኑ ባስተላለፈው መልእክት ክለቡ ወቅቱን ጠብቆ ደመወዝ ለተጨዋቾቹ እንዳልከፈለ ገልጿል። ክለቡ አስፈላጊ ክፍያዎችን በመፈጸም በተጨዋቾች ላይ የተፈጠረውን የሥነ-ልቦና እና የኢኮኖሚ ችግር ሳይቀርፍ ወደ ዝግጅት እንዲገቡ ጥሪ ያደረገበት መንገድ አግባብነት የሌለው ነው ብሎ እንደሚያምን ፌድሬሽኑ ገልጿል።

በመሆኑም ክለቡ ለተጫዋቾቹ ያልከፈላቸው ደመወዝ በአምስት ቀናት ውስጥ በአስቸኳይ እንዲፈጸም የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ማሳሰቡን ሶከር ኢትዮጵያ ዘግቧል። ይህን ተግባራዊ የማይደረግ ከኾነ ክለቡ ላይ ለሌሎችም ክለቦች ማስተማሪያ የኾነ ከባድ እርምጃን እንደሚወስድ ነው ፌደሬሽኑ ያስታወቀው።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here