“አርሰናል በአዲስ መልኩ መዋቀር ያስፈልገዋል” አሠልጣኝ ሚካኤል አርቴታ

0
322

ባሕር ዳር: ግንቦት 26/2016 ዓ.ም (አሚኮ) አርሰናል በርካታ ተጫዋቾችን እየለቀቀ ነው፡፡ የሰሜን ለንደኑ አርሰናል እንደ አውሮፓ አቆጣጠር እስከ ሰኔ 30 ቀን 2024 ውላቸው የሚጠናቀቅ 19 ተጫዋቾችን ከቡድኑ ለመልቀቅ ወስኗል፡፡ አሠልጣኝ ሚካኤል አርቴታ እንዳሉት ቡድናቸው በማንቸስተር ሲቲ ተሸንፎ የፕሪምየር ሊግ ዋንጫ ማጣቱን አስታውሰው ቡድኑ በአዲስ መልኩ መደራጀት ያስፈልገዋል ብለዋል፡፡

እስከ ሰኔ 30 ውላቸውን የሚያጠናቅቁ 19 ተጫዋቾችም እየተሰናበቱ መኾኑን ተናግረዋል፡፡ ግብፃዊው አማካኝ ሙሐመድ ኤልኔኒ ከሚሰናበቱት ተጫዋቾች አንዱ ነው፡፡ ተጫዋቹ አርሰናልን ከተቀላቀለበት ከ2016 ጀምሮ ለቡድኑ በ161 ጨዋታዎች በመሰለፍ ለረጅም ጊዜያት ግልጋሎት ሰጥቷል፡፡
ሌላው ተሰናባች ያለፈውን የውድድር ዓመት በውሰት በሬክስሃም ቡድን ያሳለፈው ግብ ጠባቂው አርተር ኦኮንኮ ነው፡፡

የቀኝ መስመር ተከላካዩ ሴድሪክ ሶሬስ በ2020 ሳውዝአምፕተንን በውሰት ተቀላቅሎ ለአምስት ዓመታት ቆይቷል፤ አሁን ደግሞ መድፈኞቹን ለመጨረሻ ጊዜ ይለቃል ነው የተባለው። ሌሎቹ የሚለቁ ተጫዋቾች ማውሮ ባንዴራ፣ ኦማሪ ቤንጃሚን፣ ሉዊስ ብራውን፣ ካታሊን ኢዮኑሺን ሲርጃን፣ ኖህ ኩፐር፣ ኦቪ ኢጄሄሪ፣ ቴይለር ፎራን፣ ግብ ጠባቂው ሁበርት ግራሲክ፣ አርተር ኦኮንኮ እና ሌሎችም ይገኙበታል ሲል ሚረር በድረ ገጹ አስነብቧል፡፡

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here