ተጠባቂው የቀነኒሳ በቀለ እና ኤሊውድ ኪፕቾጌ ፍክክር በ2024 ኦሎምፒክ!

0
426

ባሕር ዳር: ግንቦት 26/2016 ዓ.ም (አሚኮ)

ቀነኒሳ በቀለ ከ12 ዓመታት ቆይታ በኋላ ወደ ኦሎምፒክ መመለሱ የአትሌቲክስ አፍቃሪያን ትኩረት ስቧል። በፓሪስ 2024 ኦሎምፒክ ኢትዮጵያን ከወከሉት አትሌቶች ውስጥ የ41 ዓመቱ ቀነኒሳ በቀለ መካተቱ ይታወሳል። በ5 ሺህ እና 10ሺህ ሜትር የሦስት ጊዜ የኦሎምፒክ ሻምፒዮናው ቀነኒሳ በ2012 የለንደን ማራቶን አራተኛ ኾኖ ካጠናቀቀ በኋላ ብዙ ውድድሮች ላይ አልታየም።

ነገር ግን ከወር በፊት በተካሄደው የለንድን ማራቶን ተወዳድሮ ሁለተኛ የወጣው አትሌቱ የስፖርት አፍቃሪያንን ቀልብ እንደገና መሳብ ችሏል። ነሐሴ ላይ በሚካሄደው የፓሪስ ኦሊምፒክ የማራቶን ውድድር ላይ ከኬንያዊው ኤሊውድ ኪፕቾጌ ጋር ብርቱ ተፎካካሪ እንደሚኾን በርካታ የአትሌቲክሱ አፍቃሪያን ይጠብቃሉ።

የቀነኒሳ ተፎካካሪ የ39 ዓመቱ ኪፕቾጌ በ2016 ሬዮ ዴጄኔሮ እና በ2020 በቶኪዮ ማራቶን አሸናፊ ሲኾን በፓሪሱ ውድድር ለሦስተኛ ጊዜ ድሉን በጁ ለማስገባት አልሟል። በ2003 የፖሪስ የዓለም ሻምፒዮና ላይ ሁለቱ የረጅም ርቀት አትሌቶች ተገናኝተው እንደነበር ይታወሳል። በውድድሩ ኪፕቾጌ አንደኛ ሞሮኳዊው ሂቻም ኤል ጉሮጅ ሁለተኛ፣ ቀነኒሳ ደግሞ ሦስተኛ ኾነው ጨርሰዋል፡፡

በድጋሚ በ2008 ቤጂንግ ኦሎምፒክ በሁለት ውድድሮች ብርቱ ፉክክር አድርገው በ5 ሺህ ሜትር ቀነኒሳ ስለሺ ስህንን እና ኪፕቾጌን አስከትሎ አንደኛ ኾኖ አጠናቅቋል፡፡ በዚሁ የኦሊምፒክ ዘመንም ቀነኒሳ በ10 ሺህ ሜትር ድል ቀንቶታል፡፡ ከ12 ዓመታት ቆይታ በኋላ የቀነኒሳ ወደ ኦሎምፒክ መምጣቱ በአትሌቲክስ አፍቃሪያን ዘንድ ደስታን ፈጥሯል። ከኬንያዊ የሥራ ባልደረባው ጋር የሚያደርጉት ፉክክርም ከወዲሁ የብዙዎችን ቀልብ ስቧል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here