በስፔን ማድሪድ በተካሄደ የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ውድድር ዳዊት ወልዴ አሸነፈ።

0
254

ባሕር ዳር: ግንቦት 25/2016 ዓ.ም (አሚኮ)

በስፔን ማድሪድ በተካሄደ የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ውድድር በወንዶች ዳዊት ወልዴ ሲያሸነፍ በሴቶች ጥሩነሽ ዲባባ ሦስተኛ ሆና አጠናቃለች።

በወንዶች የ10 ኪሎ ሜትር ያሸነፈው ዳዊት ወልዴ 26 ደቂቃ ከ55 ሴኮንድ ገብቷል። ኬንያዊው ቪንሴንት ኪማዮ ሁለተኛ ፣ኡጋንዳዊው ማርቲን ኪፕሮቲች ደግሞ ሦስተኛ በመኾን ዳዊትን ተከትለዋል።

በሴቶች ዘርፍ ጥሩነሽ 10 ኪሎ ሜትሩን በ30 ደቂቃ ከ03 ሴኮንድ በመግባት ሦስተኛ ሆናለች ሲል ኤፍቢሲ ዘግቧል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here