አል ሂላል በኪንግ ካፕ ኦፍ ቻምፒየንስ ድል ቀንቶታል።

0
231

ባሕር ዳር: ግንቦት 24/2016 ዓ.ም (አሚኮ)

የሳውዲ ሊግ ተፎካካሪው አል ሂላል ተቀናቃኙን አል ናስርን በመለያ ምት አሸንፎ የኪንግ ካፕ ኦፍ ቻምፒየንስ ዋንጫን አንስቷል። ገና በ7ኛው ደቂቃ በሚትሮቪች ጎል መምራት የጀመሩት አል ሂላሎች መጨረስ ባይችሉም ተደጋጋሚ ያለቀላቸው የግብ እድሎችንም መፍጠር ችለዋል። በኳስ ቁጥጥርም በልጠዋል።

የአልናስር ግብ ጠባቂ ኦስፒና በሠራው ጥፋት በ56ኛው ደቂቃ ቀይ ካርድ በማየቱ ለአልሂላሎች የበለጠ ተመችቷቸው አምሽቷል። የጨዋታው ሰዓት እየተገባደደ ሲሄድ አልናስሮች ተጭነው ለመጫዎት ባደረጉት ጥረት እና በተሠራ ጥፋትና ግጭት የአልሂላል ተጫዋች አልቡላይሂ በሰከንዶች ልዩነት በሠራው ጥፋት በሁለት ቢጫ ከሜዳ ሲባረር በጥፋቱ ምክንያት ያገኙትን የቅጣት ምት አልናስሮች በያህያ አማካይነት በ88ኛው ደቂቃ ጎል አስቆጥረዋል።

በ90ኛው ደቂቃ የአል ሂላሉ ኩሊባሊ በአልናስር በረኛ ላይ በሠራው ጥፋት ደግሞ በቀይ ካርድ ተባሯል። በቁጥር አንሰው የተጫዎቱት አል ሂላሎች የአልናስሮችን ጫና ተቋቁመው 90 ደቂቃውን እና ተጨማሪ ሰዓቱን በአንድ አቻ በማጠናቀቅ ወደ መለያ ምት አቅንተዋል።
በመለያ ምትም አልሂላሎች 5 ለ 4 በማሸነፍ የዋንጫ ባለቤት ኾነዋል።

በጨዋታው አልሂላሎች ለ6 ቢጫና 2 ቀይ ካርድ ሲዳረጉ አልናስሮች 4 ቢጫ እና 1 ቀይ ካርድ አይተዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here