ባሕር ዳር: ግንቦት 23/2016 ዓ.ም (አሚኮ)
እንግሊዛዊው ማቲው ሃድሰን-ስሚዝ በኦስሎ በተካሄደው የዳይመንድ ሊግ የ400 ሜትር ሩጫ አዲስ የአውሮፓ ክብረወሰን አስመዝግቧል። አትሌቱ ርቀቱን በ44 ሰከንድ ከ07 ማይክሮ ሰከንድ በመሮጥ ነው አዲስ ክብረ ወሰን ያስመዘገበው፡፡ የ29 ዓመቱ ሃድሰን ስሚዝ ባለፈው ዓመት በቡዳፔስት በተካሄደ ውድድር ርቀቱን 44 ሰከንድ ከ26 ማይክሮ ሰከንድ በመሮጥ የዓለም ሻምፒዮና መኾኑ አይዘነጋም፡፡
አትሌቱ እንደ አውሮፓ አቆጣጠር በ2022 በአውሮፓ አትሌቲክስ ሻምፒዮናም በ400 ሜትር ርቀት አሸናፊ እንደነበርም ቢቢሲ አስታውሷል፡፡ በኖርዌይ ዋና ከተማ ኦስሎ በተካሄደ የዳይመንድ ሊግ የ400 ሜትር ሩጫ የግሬናዳው ኪራኒ ጀምስ በ44 ሰከንድ ከ58 ማይክሮ ሰከንድ፣ ሁለተኛ አሜሪካዊው ቬርኖን ኖርውድ ደግሞ በ44 ሰከንድ ከ68 ማይክሮ ሰከንድ በመግባት ሦስተኛ በመኾን አጠናቀዋል፡፡
ሃድሰን ስሚዝ እንዳለው “በጣም ተዘጋጅቼ ስለነበር እንደማሸንፍ አውቅ ነበር፤ ክብረ ወሰን በማሻሻሌ ተደሰቻለሁ” ብሏል፡፡ ውጤቱም ለፓሪስ 2024 ኦሎምፒክ የበለጠ እንዲዘጋጅ እንደሚያተጋውም ጠቁሟል፡፡ የ400 ሜትር የዓለም ዳይመንድ ሊግ ውድድር ክብረ ወሰን 43 ሰከንድ ከ03 ማይክሮ ሰከንድ በደቡብ አፍሪካዊው አትሌት ዋይዴ ቫን ኒኬርክ እጅ ተመዝግቦ እንደሚገኝ ኒውስ 24 አስታውሷል፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!