ባሕር ዳር: ግንቦት 22/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ኢትዮጵያዊው አትሌት ሀጎስ ገብረሕይወት በዳይመንድ ሊግ የ5 ሺህ ሜትር የወንዶች ሩጫ ውድድር አሸንፏል፡፡ አትሌቱ 12፡36፡73 በኾነ ሰዓት ቀዳሚ ኾኖ ሲያሸንፍ፣ የርቀቱን ሪከርድ ለመስበር በሁለት ሰከንድ ዘግይቶ መግባቱ ተገልጿል፡፡
የዓለም አትሌቲክስ መረጃ እንደሚያመላክተው አትሌት ሀጎስ በተሳተፈበት በዚህ ውድድር በታሪክ የምንጊዜም ሁለተኛውን ፈጣን ሰዓት አስመዝግቧል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!