ኦሎምፒያኮስ የኮንፈረንስ ሊግ ዋንጫን አነሳ።

0
274

ባሕር ዳር: ግንቦት 22/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የግሪኩ ኦሎምፒያኮስ የጣሊያኑን ፊዮረትኒናን ድል በማድረግ በኮንፈረንስ ሊግ ባለ ክብር ኾኗል።

በአውሮፓ ከቻምፒዮንስ ሊግ እና ከኢሮፓ ሊግ በመቀጠል ትልቁ ውድድር የኾነው የኮንፈረንስ ሊግ ትናንት ምሽት ፍጻሜውን አግኝቷል። ትናንት በግሪኳ ጥንታዊት ከተማ አቴንስ የተካሄደው የፍጻሜ ጨዋታ በኦሎምፒያኮስ ድል አድራጊነት ተጠናቅቋል። የግሪኩ ኦሎምፒያኮስ በሀገሩ በተካሄደው የፍጻሜ ጨዋታ ዋንጫውን በዚያው አስቀርቶታል። ለተከታታይ ሁለት ጊዜ ለፍጻሜ የደረሰው የጣሊያኑ ክለብ ፊዮረንቲና በሁለቱም የፍጻሜ ጨዋታዎች ተሸንፏል።

ኦሎምፒያኮስን ለክብር ያበቃችውን ግብ ሞሮኳዊው ተጫዋች አዩብ ኤል ካቢ በ116ኛው ደቂቃ ላይ አስቆጥሯል። ኦሎሚያኮስ በአውሮፓ መድረክ ያሳከው የመጀመሪያ ዋንጫ መኾኑንም ቢቢሲ ዘግቧል። ይህ ብቻ አይደለም ለግሪክ የመጀመሪያው ትልቁ ክብር ነው ተብሏል። ኦሎምፒያኮስ ድል ማድረጉን ተከትሎ ለራሱም ለሀገሩም አዲስ ክብር ጽፏል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here