ባየርሙኒክ ቪንሴንት ኮምፓኒን በአሠልጣኝነት ሾመ።

0
188

ባሕር ዳር: ግንቦት 21/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የጀርመኑ ክለብ ባየርሙኒክ ኮምፓኒን የቶማስ ቱሸል ተተኪ አድርጎ ቀጥሯል። በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ከበርንሌይ ጋር ስኬታማ የውድድር ዓመትን ያላሳለፈው ቤልጀማዊ የሙኒክ ምርጫ ኾኗል።

የሚከተለው የአጨዋወት ፍልስፍና ለክለቡ የወደፊት እቅድ ተመራጭ አድርጎታል ተብሏል። እስከ 2027 ድረስ በጀርመኑ ክለብ ለመቆየትም ፊርማውን ማስቀመጡን ቢቢሲ በስፖርት ገጹ ጽፏል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here